የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2010 ዓ.ም. በአዋጅ የተመሰረተ ተቋም ነው። ዋና ኃላፊነቱም በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን የተጣለብን የግብር ግመታ በዝቷል አሊያም አገባብ አይደለም የሚሉ ነጋዴዎችን የክስ መዝገብ በመመርመር ውሳኑኔ መስጠት ነው። ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነው።
ተቋሙ በዛሬ ዕለት የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀሙን እና በቀጣይ ዓመት ዕቅዱ ውይይት አድርጓል። በዘንድሮ ዓመት ለውሳኔ ከተቀጠሩ 719 ለ715ቱ መዛግብት ውሳኔ በመስጠት 99.4% እቅዳቸውን ማሳካት መቻላቸውን የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ተነግረዋል።
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በዘንድሮ ዓመት በጠቅላላ 1069 መዝገቦችን ተመልክቷል። ወደ ኮሚሽኑ የሚመጡ መዝገቦች የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ብቻ በመኾኑ ቁጥሩ ትልቅ እንደኾነ አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል።
በቀጣይ በከተማዋም ያሉ አሊያም በክልል የሚኖሩ ወደ ኮሚሽኑ ክሳቸውን የሚያቀርቡ ደንበኞች በበይነ መረብ መፈስጸም እንዲችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ተብሏል።
ኮሚሽኑ በፊት ላይ ለአንድ መዝገብ ውሳኔ ለመሥጠት ዓመት እና ከዚያም በላይ የሚፈጀውን ጊዜ አኹን ላይ ወደ በ6 ወር ውስጥ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ችያለሁ ብሏል። በዘንድሮ ዓመት የተካሔዱት የፍርድ ሒደቶች በገንዘብ ሲተመኑ ከ 4ቢሊዮን ብር በላይ እንሚኾኑ ተገልጿል።
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ዳኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሹሙ ሲሆን ተቋሙ ተጠሪነቱ ደግሞ ለጠቅላይ አቃቤ ሕግ መኾኑን ሰምተናል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-02
