ሀገሬ ቲቪ

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለአንድ ወር ሥራ አራዘሙ

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ወደ 2015 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እንዲቆዩ ተወሰነ፡፡

በአዋጁ ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ዝግ እንዲሆኑ እና ዳኞች ባላቸው የትርፍ ጊዜ አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን ብቻ ሊያስተናግዱ እንደሚገባ ቢደንግግም አሁን ላይ ፍርድ ቤቶቹ ለተገልጋዩ ክፍት ናቸው ተብሏል።

ፍርድ ቤቶቹ በ2014 ለ176 ሺሕ 797 ጉዳዮች እልባት መስጠታቸው ተገልጿል፡፡

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-02