ሀገሬ ቲቪ

የጋዜጠኞች እስር አሁንም አላባራም ተባለ

ሲፒጄ በኢትዮጵያ ከጥቅምት 25 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 63 ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መታሰራቸውን መዝግቧል።

ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ ስምንቱ እስከ ሐምሌ 25 2014 ዓ.ም. ድረስ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ናቸው።

ጋዜጠኝቹ በአዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና በሶማሌ ክልሎች እስር ቤቶች እንዳሉ ተጠቁሟል፤በትግራይ ያለውን የጋዜጠኞች እስር በተመለከተ ለጥናት አስቸጋሪ መሆኑንም ዓለም አቀፉ ተቋሙ በሪፖርቱ አካቷል።

ጋዜጠኞቹ ከእስር ከተለቀቁ በኋላም እንኳ በባንክ ሒሳቦቻቸውና በእንቅስቃሴዎቻቸው ላይ እገዳ እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-02