ሀገሬ ቲቪ

የኑዌር ብሔረሰብ ድጋፍ ለአማራ ክልል

የኑዌር ብሄረሰብ ዞን በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ ድገፉ ከ3ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ ነው ድጋፉ 60 የቀንድ ከብት፣ 36 ፍየሎች፣ ደረቅ አሳ እና የተለያየ አልባሳትን ጨምሮ ረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ደረቅ አሳ እና የተለያዩ አልባሳት ይገኙበታል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቦት ቴር እንዳሉት ኢትዮጵያ ለሀገሩ ክብር እና ሉዓላዊነት ህይወቱን ሳይሰሰት የሚሰጥ የጀግና ህዝብ ሀገር ስለመሆኗ ተናግረዋል። የአንድነት ሀይላችንን አሰባሰበን መሄድ ከቻልን ከውሰጥም ከውጭም የተከፈቱቡንን ሀገር የማፍረስ ሴራዎች መክተን ኢትዮጵያን ቀና የምናደርግበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ብለዋል። ድጋፉ በዞኑ ከሚገኙ አምስት ወረዳዎች የተሠበሠበ ሲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የዞኑ መንግስት እውቅናና የምስክር ወረቀትእንደተበረከተላቸው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት አስታወቋል

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-21