ሀገሬ ቲቪ

የነዳጅ ኩባንያዎች ሰነድ ካላመጡ ነዳጅ እንዳይጭኑ ትዕዛዝ ተሰጠ

የነዳጅ ኩባንያዎች ከመዳረሻቸው የመረካከቢያ ሰነድ ካላመጡ ከነገ ጀምሮ ነዳጅ እንዳይጭኑ ትዕዛዝ ተላለፈ።

የነዳጅ ኩባንያዎች፣ ነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ተሽከርካሪዎቻቸው ከጂቡቲ ነዳጅ ሲቀዱ ከዚህ በፊት የጫኑት ነዳጅ መዳረሻው ደርሶ ስለመራገፉ የርክክብ ሰነድ እንዲያመጡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ከዚህ በተጨማሪም ቦቴዎቹ ነዳጅ ቀድተው ሲወጡ ስለመዳረሻቸው ሙሉ መረጃ ለጥፈው መውጣት አለባቸው ተብሏል።

ይህ መመሪያ ከጂቡቲ እስከ ማደያ ድረስ ይፈጸማል የሚባለውን የኮትሮባንድ ንግድ ለማስቀረት አስተዋጾ እንደሚኖረው ታምኗል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-03