ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ በኬንያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሚቀጥለው ሳምንት ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት የአሜሪካ ዜጎች ወደ ሀይቅ ዳር ወደምትገኘው ኪሱሙ ከተማ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።

በመግለጫዉ በምዕራብ የኬንያ ከተማ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሰልፎች ሊደረጉ እንደሚችሉ እና አንዳንዴም ወደ ሁከት ሊቀየሩ እንደሚችሉ ተንብየዋል።

ፖሊስ ትላንት ስምንት ሰዎችን ከጥላቻ በራሪ ወረቀቶች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተናግሯል፡፡

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-03