
የሱማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞ የአልሸባብ መሪ ሙክታር ሮቦውን የሀይማኖት ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።
የአልሸባብ እስላማዊ ቡድን ምክትል መሪ እና ቃል አቀባይ የነበሩት ሙክታር ሮቦው “በትምህርት፣ በልምድ፣ በታሪካቸው እና ፍትሃዊነታቸው የመረጥኳቸውን አዲሱን ሰው ሳቀርብ በደስታ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ በሹመቱ ላይ ተደምጠዋል።
በአንድ ወቅት አሜሪካ ይህንን ሰው ለያዘልኝ 5 ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው፤ ሮቦው በሐምሌ 2009 ዓ.ም ከአሸባሪ ቡድኑ ጋር ያለኝ እህል ውሃ አብቅቷል ብሏል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-08-03