ሀገሬ ቲቪ

ደቡብ ኮሪያ የጦር መሳሪያ ሽያጯን የማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ተጠቆመ

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት እና የጦር መሳሪያ አምራቾች የተሻሻሉ የጦር መሳሪያዎችን በማምረት እንዲሁም የውጭ ንግድን የማሳደግ ፍላጎት አላቸው ሲል ዲደብሊው ዘግቧል።

የጦር መሳሪያ ሽያጯ በዚህ ዓመት ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ሊል ይችላል። ደቡብ ኮሪያ በታሪኳ ትልቁን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት ከፖላንድ ጋር አድርጋለች ።

በሩስያ ዩክሬይን ጦርነት ከዩክሬይን ጎን ከቆመችው ፖላንድ ጋር በተደረገው የሽያጭ ስምምነት ታንኮች፣ ከባድ የጦር መሳሪያዎች እና ተዋጊ ጀቶች ተካተዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-08-03