44ተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው አፍሪካ አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ናቸው። እኒህ ሰው የተወለዱት ታዲያ በዛሬዋ ዕለት በ1954 ዓ.ም. ነበር።
የመጀመሪያው አፍሪካ አመሪካዊ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው ባሻገር የኖቤል የሰላም ሽልማትንም በ2002 ዓ.ም. ማግኘት ችለዋል። አሜሪካን ለሁለት የምርጫ ጊዜም በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።
ዓለም አቀፍ ግንኙነትን ለማጠናከር እና በህዝቦች መካከል መቀራረብን ለማምጣት በመስራታቸው በሚል ነበር በ2002 ዓ.ም. የኖቤል ሽልማት የተበረከተላቸው።
ከኩባ፣ ኢራን እና ቬንዝወላ ላደረጉት የመቀራረብ ንግግር ብሎም የአሜሪካ ወታደሮችን ከኢራቅ በማስወጣት ለሰላም ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በሙሉ ስማቸው ባራክ ሁሴን ኦባማ ተብለው የሚጠሩት ባራክ ኦባማ የተወለዱት በአሜሪካ ሃዋይ በሆኖሉሉ በዛሬዋ ዕለት በ1954 ነበር። የኦባማ አባት በኬንያ የገጠር አካባቢ የፍየል እረኛ የነበሩ ናቸው። ወደ አሜሪካ የትምህርት ዕድል አግኝተው ከሄዱ በኋላ ተመልሰው ሀገራቸውን በኢኮኖሚ ባለሙያነት አገልግለዋል።
የኦባማ እናት አን ዱናንም በዚያው አሜሪካ አግኝተዋቸው ተጋብተው ባራክ ኦባማን አፍርተዋል።
አባቱ እናቱ በመለያየታቸውም ኦባማ ከእናታቸው ጋር ለማደግ ተገደዋል። ከታናሽ እህታቸው ማያ ጋርም አብረው አድገዋል።በመንግስት ትምህርት ቤትም ትምህርታቸውን መከታተል ጀመረዋል። ለአጭር ጊዜ የኦባማ እናት ምግባቸውን ከመንግስት ድጎማ የሚያገኙ ነበሩ። ቢሆንም ግን አኗኗራቸው የመካከለኛ ገቢ የሚባል ነበር።
ኦባማ በተወለዱባት ሆኖሉሉ የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከሎስ አንጀለስ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ኦክሲደንታል ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ በኒው ዮርክ ሲቲ ወደሚገኘው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተዛወሩ፤ በዚያም በ1975 ዓ.ም. በፖለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውም የስነ ጽሁፍ እና የፍልስፍና መጻህፍትን ያነቡ ነበር።
የቢዝነስ ኢንተርናሽናል ድርጅት ጸሃፊ እና አዘጋጅ በመሆንም ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል። ኋላም በአብዛኛው በድህነት በተጠቃው በቺካጎ በፋር ሳውዝ ሳይድ በማህበረሰብ አደራጅነት አገልግለዋል።
ከሶስት ዓመታት በኋላ በ1986 ዓ.ም. ወደ ትምህርት ተመልሰውም በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ህግ ተከታትለዋል።
በዚያም የመጀመሪያው አፍሪካ አሜሪካዊ የሃርቫርድ የህግ ጥናት ት/ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል። በህግ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ወደ ቺካጎ በመጓዝ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ንቁ ተሳታፊ ሆነዋል።
በኢሊኖይስ ቢል ክሊንተን እንዲያሸንፉም ለመምረጥ አስር ሺዎች እንዲመዘገቡ አድርገዋል። የፖለቲካ ተሳትፏቸውን እያሳደጉ ባለበት በዚሁ ጊዜ ‘’Dreams of My Father’’ (የአባቴ ህልሞች) የተሰኘው መጽሃፋቸውን ለንባብ አብቅተዋል።
የፖለቲካ ግስጋሴያቸውም አንድ አለ። የኢሊኖሲስ ግዛት ፕሬዝዳንት ተደርገው በ1988 ዓ.ም. ተመረጡ። በስልጣን ዘመናቸውም የፋይናንስ መረጋጋትን፣ ለድሃ ቤተሰቦች የጤና እንክብካቤ ድጋፍ እንዲስፋፋ ብሎም የወንጀል እና ደህንነት ህጎች እንዲሻሻሉ ማድረጋቸውም ይወሳላቸዋል።
ኋላም በ1996 ዓ.ም. ለአሜሪካ ምክር ቤት ተመረጡ። ለአሜሪካ ምክር ቤት ምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉት ንግግርም ሰፊ እውቅናን አሰጥቷቸዋል። በፓርቲያቸው ውስጥም በፍጥነት እውቅ ሰው እስከመሆንም ደረሱ።
በዚያው ዓመት ወደ አባታቸው ሀገር ኬንያ ያደረጉት ጉዞም የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት መሳብ ችሎ ነበር።
በ1999 ዓ.ም. የኢሊኖሲስ ፕሬዝዳት የሆኑት ባራክ ኦባማ የአሪዞና አቻቸው ጆህን ማኬይን በማሸነፍ 44ተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅተዋል። በዚህም የመጀመሪያው አፍሪካ አሜሪካዊ የነጩ ቤተ መንግስት ፕሬዝዳንት ለመባል በቁ።
በ2006 ዓ.ም. ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው አሜሪካን አገልግለዋል። ኦባማ በበሳል የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው፣ ለአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ቀውስ በሰጡት ምላሽ እና የጤና ዋስትና ፕሮግራማቸው ይበልጥ ይወሳሉ። ኋላም በዶናልድ ትራምፕ በ2009 ዓ.ም. ተተክተዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-08-04
