
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠር የምታደርገው ተግባር አጸያፊ ነው ሲል ኮንኗል።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ የታይዋን ጉብኝት ተከተሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰተሩ ባውጣው መግለጫ ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ እንደሆነም አበክሮ ገልጿል።
የቻይና መንግሥት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም ፖሊሲዎችን የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነውም ተብሏል።
ይህ መረጃ እነከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ኤርትራ የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ያወገዘች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ስትሆን ሩሲያ እና ሰሜን ኮርያም ሃሳቡን ይጋራሉ።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-04