የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት ዋና ጸኅፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የነዳጅና የጋዝ ኩባንያዎች በድሃው ሕዝብና በአየር ንብረት ላይ ኪሳራ በማድረስ ከፍተኛ ትርፍ እያጋበሱ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ሥነ ምግባር በጎደለው ድርጊታቸው በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጊዜ ውስጥ ትልልቆቹ የኃይል ማመንጫ ኩባንያዎች ጠቅላላ ትርፍ ወደ 100 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ተጠግቷል።
እነዚህን ከልክ ያለፉ ትርፎች በሙሉ ግብር በአግባቡ እንዲከፈሉ እና ገንዘቡን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የደከሙ ሰዎችን ለመርዳት እንዲጠቀሙበት አሳስባለሁ ብለዋል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-04
