ሀገሬ ቲቪ

የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ የ’ትራፊክ መብራት

በዕለት ከዕለት እንቅሳሴዎቻችን የምገለገልባቸው የሰው ልጅ የስራ ውጤቶች የተጀመሩበት የሆነ ጊዜ አላቸው። ዛሬ በዕለቱን ከታሪክ የመነገዶችን የተሽከርካሪዎች እሽቅድምድምን በመግታት አደጋዎችን ለመቀነስ ስለሚያገለግለን የትራፊክ መብራት እንነግራችኋለን።

የትራፊክ መብራት በመኖሩ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባቸው ከተሞች ስንት አደጋዎች ቀንሰዋል። ዛሬ ታዲያ በ1906 ዓ.ም. የመጀመሪያው የኤለክትሪክ የትራፊክ መብራት አገልግሎት ላይ የዋለበት ነበር።

የከተሞች መስፋፋት እና የተሽከርካሪዎች ቁጥር መጨመር በመንገዶች ላይ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ ምልክቶች አስፈላጊ ነበሩ። ለዚህም የትራፊክ መብራት አስፈላጊነትን ያጤኑ ሰዎች የትራፊክ መብራትን ለመስራት እና ለማሻሻል ጥረዋል።

የትራፊክ መብራት ግኝትም የዓለም የተሽከርካሪ መንገዶች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ቀንሷል። 108 ዓመታትን ወደኋላ መለስ ስንል ታዲያ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ የትራፊክ መብራት ስራ ላይ መዋሉን እናገኛለን።

ይሄው የመጀመሪያ የኤለክትሪክ የትራፊክ መብራት አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረው በአሜሪካ ክሌቨላንድ በኦሃዮ ግዛት ነበር።

የትራፊክ መብራቱ አገልግሎት ላይ መዋሉ የመንገዶችን ልማድ ቀይሯል። በመጀመሪያዎቹ የአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር ሁከት የበረከተበት ነበር። እግረኞች፣ ብስክሌቶች፣ ፈረሶች፣ ጋሪዎች ጭምር በቀኝ የመንገድ ክፍል በኩል ከሞተር ተሽከርካሪዎች ጋር ይፎካከሩ ነበር።

የጋሪዎች ቁጥር እያደር መቀነሱ የመንገድ መጨናነቁን በተወሰነ መንገድ ቢያቀለውም የመንገድ መጨናነቁን እና በመንገዶች ላይ የሚደርሰውን አደጋ የሚቀንስ አሰራር ያስፈልግ ነበር። ለዚህም መንገድ መክፈል፣ ምልክቶችን ወደ ግራ መታጠፍ አይቻልም የመሳሰሉትን መጠቀም ተጀመረ።

ኋላም አንድ ክፍለ ዘመን መለስ ስንል የመጀመሪያው የኤለክትሪክ የትራፊክ መብራት አገልግሎት ላይ ዋለ። በ1906 ዓ.ም. በዛሬዋ ዕለት በኦሃዮ ክሌቨላንድ አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረው ይሄው የትራፊክ መብራት አረንጓዴ እና ቀይ መብራቶችን ሲጠቀም ቢጫው መብራት ግን አልነበረውም።

የቢጫ መብራቱን ሚና ግን ደዎሎች እንዲተኩ ተደርጎ ነበር። በ1910ዎቹ ግን ቢጫ መብራቱ ተጨምሯል። ኋላም ወደ ሌሎች ከተሞች ተሰራጭቷል።

የዚሁ የተሻሻለ እና በኤለክትሪክ የሚሰራ የትራፊክ መብራት የፈጠራ ባለቤት ጋሬት ሞርጋን ይሰኛል። ለዚሁ ፈጠራውም በ1915 ዓ.ም. የፈጠራ ባለቤትነቱን ይዟል። ኋላም ለጀነራል ኤለክትሪክ የባለቤትነት መብቱን ሽጦታል።

ይሄው የትራፊክ መብራት ቀደም ካሉ እና በአውሮፓ ምድር ለአጭር ጊዜ ካገለገሉ እንደበጋዝ ላይት የሚሰሩ የትራፊክ መብራቶች ካሉት የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል። እንግሊዝ የመጀመሪያ የኤለክትሪክ የትራፊክ መብራቶችንም በ1915 ዓ.ም. አገልግሎት ላይ ማዋል ጀመራለች።

በአብርሃም በለጠ
2022-08-05