ሀገሬ ቲቪ

የሴኔጋል ገዥው ፓርቲ የፓርላማውን አብላጫ ድምጽ አጣ

የሴኔጋል ገዥ ቤኖ ቦክ ያካር ጥምረት በተካሄደው የሕግ አውጭ ምርጫ ሁለት መቀመጫዎችን ብቻ በማግኘቱ የፓርላማውን አብላጫ ድምጽ አጥቷል።

በጎጎሮሳውያኑ በ1960 የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ነፃነቷን ካገኘች በኋላ የሴኔጋል ገዥ ፓርቲ በፓርላማ ያለውን አብላጫ ድምፅ ሲያጣ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ዋናው የተቃዋሚው ጥምረት ኢዊ አስኬን 56 መቀመጫዎችን ሲያገኝ፣ አጋራቸው ዋሉ ሴኔጋል 24 መቀመጫዎችን አሸንፏል።

በምርጫው ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ሴኔጋላውያን ተሳትፈዋል፤ 8 ጥምረቶች ለምርጫ ቀርበው ነበር። የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛ እንደዘገቡት በሀገሪቱ ውጥረት ነግሷል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-05