መቀመጫውን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ያደረገው Gulf Ingot FZC የተሰኘ ድርጅት ለተለያዩ የመጠጥ እና የውሃ ማሸጊያነት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎችን ለማምረት የሚያገለግሉ ምርቶችን ለማምረት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
ድርጅቱ በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ 11 ሺሕ ሜትር ካሬ ሼድ በመከራየት ነው ስራውን የሚሰራው።
ለዚህም 5 ነጥብ 26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የሚያደርግ ሲሆን ከ139 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሆነ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
ኩባንያው አሁን ላይ በኬንያ እና ሩዋንዳ ፕሮጀክቶችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-05
