ሀገሬ ቲቪ

12 ሰዓታትን በዋና ያሳለፉት ሚኒስትር

የማዳጋስካር ሚኒስትር 12 ሰዓታትን በመዋኘት ህይወታቸውን አተረፉ፡፡ ትረፊ ያላት ነፍስ እንዲሉ አንዳንዶች በከባድ አደጋ ውስጥ አልፈው ህይወታቸው ይተርፋል አንዳንዶች ደግሞ ስንጥር ወግቷቸው የሚበሉት አንቋቸው ህይወታቸው ጸጥ ትላለች፡፡ በማዳጋስካር የተሰማው ለማመመን የሚከብድ ነው፡፡ የማዳጋስካር መንግሥት ሄሊኮፍተራቸው በነፍስ አድን ተልዕኮ ላይ በነበረበት ጊዜ መከስከሱ ተሰምቷል ፡፡ ከመከስከሱ ባለፈ ባህር ላይ መከስከሱ ደግሞ አደጋውን የከፋ አደረገው ፡፡ ሂሊኮፍተር ተከስክሶ በድንገት ሰው ሊተርፍ ይችል ይሆናል ከዚያ የባሰው ግን ባህር ውስጥ መከስከሱ ነበር፡፡ በውስጡ የነበሩ የሀገሪቷ ሚኒስትር እና የደህንነት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ ታዲያ የፖሊስ ሚኒስትሩ ለ12 ሰዓታት በመዋኘት በህይወት መትረፋቸው አጀብ አሰኝቷል፡፡ የፖሊስ ሚኒስትር ሰርጌ ገሌ ከብዙ ውጣውረድ በኋላ መትረፋቸው ተዓምር ሲሆን "የምሞትበት ጊዜዬ አይደለም" ሲሉ የተናገሩበት የተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የብዙሃን መገናኛ ተሰራጭቷል፡፡ በሄሊኮፕተሩ አብረዋቸው ሲጓዙ የነበሩ ሌሎች ሁለት የደህንነት ባለስልጣናትም ከአደጋው ተርፈዋል፡፡ በፖሊስ ሚኒስትሩ የተመራው ቡድን በሰሜናዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የመንገደኞች ጀልባ የሰመጠበትን አካባቢ ሲቃኝ ነበር አደጋ የደረሰበት፡፡ በሰመጠው ጀልባ 39 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የሀገሪቷ ፕሬዝደንት አንድሪ ራጆኤሊና በትዊተር ገፃቸው ላይ ህይወታቸውን ላጡት ሀዘናቸውን በመግለፅ ለሚኒስትሩ እና ለሌሎች ሁለት መኮንኖች ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-22