የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አገራችንን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት ላይ ያለ ችግር መሆኑ ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ እጥረትና መሰል ችግሮች የትራንስፖርት ዘርፉ ማህበረሰቡን በ አግባቡ እንዳያገለግል ምክንያት ሆኗል።
ይህን በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚስተዋልን ችግር ለመቅረፍ ዛይራይድ እና ወዝ የተባሉ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የኮድ ሁለት ተሽከርካሪዎችን በስራ መውጫ እና በስራ መግቢያ ሰአት ፣ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ አመቻችተው ወደ ስራ ሊገቡ መሆኑን አስታውቀዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ ከ100,000 በላይ የኮድ 2 መኪኖች ያሉ ሲሆን ፣ እነዚህን መኪኖች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡበት መንገድ መመቻቸቱ ፣ ለከተማው የትራንስፖርት ችግር መፍትሄ ከማምጣቱ ባለፈ ፣ ለመንግስት በአመት ከታክሲ ዘርፉ የሚሰበስበውን ግብር ከ 3 ቢሊዮን እስከ 6 ቢሊዮን ብር ሊያደርሰው እንደሚችል የዛይራይድ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ኘሮግራሙን ባስታወቁበት መድረክ ላይ ገልጸዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-05
