የዓይን ብሌን ጠባሳ በተፈጥሮ አሊያም ከጊዜ በኋላ የሚከሰት የዓይን ብሌን ላይ ጠባሳ በመጣል ለዓይነስውርነት የሚዳርግ ነው።
በአይን ብሌን ጠባሳ በሚመጣ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያት የሚከሰት አይነስውርነትን በመታደግ ብርሃናቸው እንዲመለስ ትኩረቱ አድርጎ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የአይን ባንክ 19 ዓመታትን አስቆጥሯል።
በትብብር ከዓይን ባንኩ ጋር የሚሰሩት በኤልአሚን የሕክምና ማዕከል ውስጥ የአይን ሕክምና ስፔሻሊስትና የዓይን መስታወት ሰብስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ኤልያስ ኃይሉ ዓይናችን ንጹህ የሆነ ብርሃን የማስተላልፊያ ክፍላችን ነው ይላሉ።
ንጽሁ የዓይን ክፍላችን ጠባሳ ከጣለበት፣ ደም ስር ከበቀለበት እንዲሁም ከሳሳ ስራውን መስራት አይችልም በዚህ ምክንያት እይታ ሊቀንስ አሊያም ሙሉ ለሙሉ ሊጠፋ ይችላል ይላሉ ዶክተሩ። በተለይ ከጥንቃቄ ጉድለት የሚመጡትን ጠባሳዎች መከላከል ተገቢ መሆኑን በማንሳት ።
በኢትዮጵያ ከ 300 መቶ ሺሕ በላይ የዓይን ነቅለ ተከላን የሚጠበቁ ዜጎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ሁሉም ንቅለ ተከላውን ያካሂዳሉ ባይባልም እንኳን የለጋሾች እጥረት በመኖሩ በርካታ ዓመታትን የሚጠብቁ ብዙዎች መሆናቸውን ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ከህልፈት በኋላ ከለጋሽ ላይ ብሌንን በመሰብሰብ ፈተሻ በማደርግ ፣ሕክምናው ለሚሰጡ ተቋማት ከማሰራጨት ባለፈ በዓይን ብሌን ጠባሳ የተጎዱ ወገኖችን ብርሃናቸው እንዲመለስ በጎ ለጋሾችን እንዲበረከቱ ማህብረሰቡን ማንቃት ዓላማው አድርጎ ተቋቁሟል።
ሕብረተሰቡ ይህንን ዓላማ ካለመረዳት እና ከግንዛቤ እጥረት በሚፈለገው ልክ ባለመለገሱ በርካቶች የአይን ብሌንን ንቀለ ተከላ እንዲደረግላቸ ወረፋ ይዘው ቁጭ ብለዋል።
አንዳንዶች የፊት ገጽታ ያበላሻል በሚል የሚቀየርው ሙሉ አይን የሚምስላቸው እንዳሉም ለመረዳት ችለናል። በተጨማሪም የሃይማኖት አስተምሮትን ካለመረዳት ፣ቃል የገባው ሰው አላማው ገብቶት ቢሆንም ከህልፈተ በኋላ ቤተሰብ አለማሳውቅ ችግር፣ የተቋሙ በክልሎች ማዕከላት ያለመክፈት ተዳምረው ለአይን ብሌን መሰብሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚያደርስ እንደሆነ ተገልጿል።
በርካቶች በዚሁ ችግር እየተሰቃዩ እንዳሉ በመገንዝብ ዜጎች የአይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-08-08
