ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል ።
የደኅንነት ምክር ቤቱ ሰኔ 1 አካሂዶት በነበረው ስብሰባ በአስቸኳይ ለማከናወን ውስኗቸው ከነበሩት ተግባራት መካከል 3 ሺህ 180 የሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፤ በሸኔ ተይዘውና ፈርሰው ከነበሩ 1 ሺህ 739 ቀበሌዎች መካከል 1 ሺህ 255 ያህሉ እንደገና መደራጀታቸውን አስታውቋል።
ምክር ቤቱ በቀጣይም አሸባሪና ሕገ ወጥ ታጣቂዎችን ሥጋት ከማይሆኑበት ደረጃ ማድረስ፣ ሕዝቡን በሚያማርሩ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ የሙስና፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወዘተ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለሕዝቡ ዘላቂ መፍትሄ ማበጀትን ወስኖ እየሰራ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-08
