ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ህብረት እስራኤልን አወገዘ

የአፍሪካ ህብረት እስራኤል በጋዛ የፈጸመችውን የአየር ጥቃት ኮነነ ። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ህብረቱ ከፍልስጤማውያን ጎን እንደሚቆም በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

በአየር ጥቃቱ 6 ህጻናትን ጨምሮ ከ30 በላይ ንጹሃን ህይወታቸውን እንዳጡ ታውቋል። በእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች የቀጠለው ህገወጥ ይዞታዎችን የማጠናከር እርምጃ ከዓለምአቀፍ ህግጋትጋር እንደሚጻረር በመግለጫው ተነስቷል።

ፍልስጤም ምስራቃዊ እየሩሳሌምን በዋና መቀመጫነት ይዛ ሉዓላዊት ሃገር ለመሆን የምታደርግውን ጥረት ህብረቱ እንደሚደግፍ ጠቁሟል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-08