ሀገሬ ቲቪ

አንበጣ ካንሰርን መለየት ቻለ

አራት ፊደል፤ ዓለምን የሚያስጨንቅ በሽታ፤ ካንሰር የሚለው ስም ደግሞ መጠሪያው ነው። በየዓመቱ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በዚሁ በሽታ ሳቢያ ይህችን ዓለም ይሰናበታሉ።

ይህም ከስድስት ስዎች ሞት የ አንዱ በዚሁ በሽታ ሳቢያ የሚመጣ ነው። በ2012 ዓ.ም በመላው ዓለም ቨሚሊየን የሚጠጉ የካንሰር ታማሚዎች እንደሚኖሩ ይታመን ነበር።

በቅርብ ጊዚ የቀረቡ ጥናቶች እና የተረጋገጡ ቁጥራዊ መረጃዎች ባይገኙም የተጠቂዎች ቁጥር ግን ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል።

ይህ የዓለም ፈተና የሆነው ካንሰር ተጠቂዎች 30 በመቶ የሚሆኑት በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ እና በድህነት በሚማቅቁ ሀገራት ውስጥ እንደሚገኙም የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

የዘርፉ ተመራማሪዎች ይህን በሽታ ለማከም መላውን ፍለፍጋ በቤተሙከራዎች ውስጥ መልፋት ከጀመሩ ዘመናትን ተሻግረዋል። ታዲያ ይሄው መታተር ውጤት ማምጣት መጀመሩን ከወደ አሜሪካ ሰማን እና ልናጋራችሁ ወደድን።

የሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከፍጥረታት ዓለም ትንሽዬዋ አንበጣን በመጠቀም ካንሰርን መለየት ችለናል ብለዋል። እንደተመራማሪዎቹ ከሆነ አንበጣ ካንሰር ያለበትን እና የሌለበትን ሰው በማሽተት ብቻ መለየት ትችላለች።

ውጤቱን በተስፋ የሚሞላ የሚያደርገው ደግሞ ይህችው በራሪ ፍጥረት ካንሰሩ ገና ሳይጎለብት በለጋ እድሜ ላይ እያለ መለየት መቻሏ ነው።

ማሽተት እና መለየት ብቻም ሳይሆን የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን ማወቅ መቻሏ ደግሞ አጃኢብ አሰኝቷል። አንበጣዋ ካንሰር ያለበትን ሰው ትንፋሽ ስታሸት በአንጎሏ ውስጥ ከተለመደው ውጪ የሆነ ኬሚካሎችን በማመንጨት ለመለየት ትጠቀምበታለች። ይህም ካንሰርን ለመለየት የተሻለ አማራጭን የሚጠቁም እንደሆነ ተነግሮለታል።

ተመራማሪዎች ከ15 ዓመታት በላይ ካንሰርን ለመለየት የሚያስችል መሳሪያን ለመስራት በምርምር ላይ ቢቆዩም ይህኛው ግን በጣም በአጭር ግዜ ውጤቱን ማወቅ የሚቻልበት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ካንሰርን በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ ሳለ በአጭር ግዜ ውስጥ መለየት መቻል ከካንሰር ለማዳን ትልቅ አቅምን የሚፈጥር እንደሆነም ተነግሮለታል።

ታዲያ ተመራማሪዎቹ ነፍሳቱ ካንሰርን ለመለየት የተጠቀመበትን ጥበብ በመውስድ ካንሰርን የሚለይ ማሽንን ለመስራትም አቅደዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-08-08