ሀገሬ ቲቪ

የእዳ መክፈያ ጊዜ የተራዘመላት ኢትዮጵያ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሀገራት እዳ አራዘመ፡፡ የዓለም ገንዘብ ድርጅት (IMF) አነስተኛ ገቢ ላላቸው 25 ተበዳሪ ሀገራት ተጨማሪ የእዳ አገልግሎት መክፈያ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ እዳ መክፈያ ጊዜው ለ3 ወር በማድረግ ለ25 ሀገራት ነው ማራዘም የቻለው፡፡ እዳው ከተራዘመላቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን 20ዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡ የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ተሰብስቦ ባሳለፈው ውሳኔ 25ቱ ሀገራት ለድርጅቱ መክፈል የሚገባቸውን ክፍያ በሦስት ወር አራዝሞታል፡፡ ድርጅቱ የእዳ መክፈያ ጊዜ ሲያራዝም ይህ ለ5ኛ ጊዜ ሲሆን የመጨረሻው መሆኑን አሳውቋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ 4 ጊዜ የእዳ መክፈያ ማራዘሚያ ጊዜ ሰጥቶ ነበር፡፡ በድምሩ 964 ሚሊዮን ዶላር የእዳ እፎይታ ተሰጥቷል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-22