ሀገሬ ቲቪ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዘመናዊ የክፍያ ሰርአትን ልተገብር ነው አለ

በ2014 በጀት ዓመት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት 1 ነጥብ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል ተባለ።

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክር አቶ ሙሉቀን አማረ ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ከሰጠው አገልግሎት ያገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ50 በምቶ በላይ ጭማሪ ።

በቀጣይም ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያ በእጅ ስልክ ወይም በኦንላይን ማከናወን የሚችሉበት አሰራር ተግባራዊ ሊያደረግ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-09