የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተደረገው የነዳጅ ድጎማ የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ ግብረ ሀይል ተቋቋመ ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እየተደረገ ያለው የነዳጅ ድጎማ በታለመው ልክ ውጤታማ እንዲሆን በአፈፃፀም ሂደቱ የታዩ ክፍተቶች በፍጥነት እንዲስተካከሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የተቋቋመው ግብረሐይል አባላት ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ፣ ከከንቲባ ፅ/ ቤትና ከቴሌኮሙኒኬሽን ያካተተ መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-09
