ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ 20 ሺህ አባዎራዎች የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ።
ኤን ፒ ኤስ የተሰኘ የአፈር ማዳበሪያ እና ዩሪያ ድጋፍ የተደረገላቸው አርሶ አደሮች በማዕከላዊ ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ የሚገኙ መሆናቸውን ከኮሚቴው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ድጋፉ በግለሰብ ደረጃ 120 ሺህ ገደማ የሚደርሱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚያስችል ተጠቁሟል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-09
