የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ ጋር የ165.2 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ እና ብድር ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ በበይነ መረብ በተካሄደ ውይይት የተፈጸመ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስምምነቱ የተደረገው የመሬት መራቆትን በመቀነስ ምርታማነትን ለሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንደሆነ ተጠቁሟል።
58 ሚሊዮን ዶላር ያክሉ በእርዳታ የተገኘ ሲሆን 107 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው በረዥም ጊዜ የሚከፈል ብድር ነው ተብሏል።
በአብርሃም በለጠ
2022-08-10
