ሀገሬ ቲቪ

ክርስቶስን ማምለኪያ የነበረው ቀለበት መገኘት

የጥንት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን ለማመልከት ይጠቀሙበት የነበረው የወርቅ ቀለበት ተገኘ፡፡ ‹‹መልካም እረኛ›› የሚል ስያሜ ያለው ቀለበቱ በግ በትከሻው ላይ የተሸከመ የእረኛ ምስል የተቀረጸበት ነው፡፡ ምስሉ አረንጓዴ የከበረ ድንጋይ ላይ የታተመ እና በወርቅ ቀለበቱ በላይኛው ክፍል ላይም በጉልህ ይታያል፡፡ በሮማውያን ዘመን በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ነውም ተብሏል፡፡ በከበረ ድንጋይ ያጌጠው የወርቅ ቀለበቱ በእስራኤል ሜዲትራኒያን የባሕር ዳርቻ ላይ በአርኪኦሎጂስቶች እንደተገኘ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡ ቀለበቱ በጥንቷ ቂሳርያ ወደብ አቅራቢያ በተከሰቱት ሁለት የመርከብ አደጋዎች ከተገኙት በርካታ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በዚህ ጥናት በ3ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የብር እና የነሐስ የሮማውያን ሳንቲሞች እንዲሁም ከ14ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ በማምሉክ ዘመን የነበሩ ብዙ የብር ሳንቲሞች ያካትታሉ፡፡ በተጨማሪም እርኩሳን መናፍስትን ለማስወገድ ይጠቀሙበት የነበረ የነሐስ ደወሎች እና በቀይ የከበረ ድንጋይ በበገና መልክ የተቀረጸ ቀለበትም ተገኝቷል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-23