ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግስታት ጥያቄ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት

አምስት ወራትን የዘለቀው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት አንዴ ሞቅ ሌላ ግዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ እንደቀጠለ ነው ። በተለይ ሁለቱም ኒኩለርን ኃይል ማመንጫነት የሚጠቀሙ መሆናቸው በጦርነቱ ሳቢያ በእነዚህ ኒውክሌየር ማብላያ ጣቢያዎች ላይ ኧንዳች ጉዳት ቢደርስ ችግሩ ለዓለም ይተርፋል በሚልም ኧብዛኞች ጭንቅታቸውን ይገልጣሉ።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ በዩክሬይን እና ሩሲያ መካከል ውዝግቦችን እያስነሳ የሚገኘውን የዛፖርዢያ ኒውክሌየር ማብላያ ጣቢያ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተወጣጡ ተቆጣጣሪዎች እንዲከታተሉት ፍቃድ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉትም ለዚሁ ነው።

ዛፓርዢያ በዩክሬን የሚገኝ በአውሮፓ ትልቁ ኑውክሌየር ማብላያ ጣቢያ ሲሆን አሁን ላይ ግን ሩሲያ ከተቆጣጠረችው ወራቶች ተቆጥረዋል ።

ዋና ጸሀፊው በሩሲያና በ ዩክሬን መካከል የሚደረገውን የኒውክሌር ውዝግብ በማውገዝ

“ማንኛውም የኒውክሌየር ጥቃት ራስን በራስ ማጥፋት ነው። ስለዚህም አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ተቆጣጣሪ ድርጅት አለም ላይ የሚገኙትን የኒውክሌፍ ማብላያ ጣቢያዎች በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ሊያደርጋቸው ይገባል ። ተመድም የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነው” ብለዋል ።

ዩክሬን ሩሲያ ሦስት የጨረር ማዕከላቶቼን ከማውደም በተጨማሪ በተከታታይ ሁለት ቀናት ባደረገቸው ጥቃት የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞቼን ጎድታብኛለች በማለት ስትከስ ቆይታለች።

የዩክሬን አምባሳደር ዪቪኒ ሲምቦሊክም ጉተረስ ለአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ተቆጣጣሪ ድርጅት ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበል የሩሲያን ሀይሎች በፍጥነት ሊያስቆሟቸው ይገባል ብለዋል ።

አምባሳደሩ የሩሲያ ሀይሎች ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የተቆጣጠሩትን የዩክሬን የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ በመጠቀም በደቡባዊ ዩክሬን ክፍል ውስጥ የኤሌክትሪክ ሀይሎችን ከማጥፋት ጀምሮ ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ አስበዋል።

ለዚህም ተግባር በማዕከል ውስጥ የነበሩ ዩክሬናዊያን ሰራተኞችን በ አፈሙዝ በማስፈራራት ቀን ከለሊት እያሰሯቸው ነው ብለዋል ።

የዩክሬን የኑክሌር ኃይል ኩባንያ ኤነርሃቶም ኃላፊ የሆኑት ፔትሮ ኮቲንም በአካባቢው ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ የሆነ ዞን መፈጠሩ እና የሰላም አስከባሪ ሀይሎች መኖራቸው “ይህን ችግር ይፈታዋል” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪም ባሳለፍነው እሁድ በ ሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ባስተላለፉት መለዕክት ሩሲያ አለም አቀፍ ማዕቀብ ሊደረግበት የሚገባውን “የኒውክሌር ሽብር” ፈጥራለች ሲሉ ድርጊቱን ኮንነውታል ።

ዘሌንስኪ “አሸባሪ መንግስት በኒውክሌር ጣቢያ ላይ ሲተኩሰ ደህንነት ሊሰማው የሚችል እንደዚህ ያለ ህዝብ በአለም ላይ የለም” ብለዋል።

ታዲያ ፕሬዝዳንቱ ያሳለፍነው እሁድ ይሄን ቢናገሩም ዛሬ ላይ ክሪሚያን ሳናስመለስ ጦርነት ይቆማል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው ማለታቸውን ቢቢሲ በፊት ገጹ አስነብቧል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-10