በኢትዮጵያ የሚኖሩ ከ750ሺ በላይ ስደተኞችን ለመመገብ 73 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ።
በድርጅቱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ክላውድ ጂቢዳር እንዳሉት ድጋፉ በአፋጣኝ የማይገኝ ከሆነ ስደትኞቹ ለከፋ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ። ለችግሩ መከሰት ምክንያት የሆነው ከ2015 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የኮታ ቅነሳ መጠኑ አሁን ላይ 50 በመቶ ድረስ በመውረዱ ነው።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ክላውድ ጂቢዳር ድጋፉ የማይስተካከል ከሆነ ስደተኞቹ ደህንነታቸው ሳይጠበቅ ወደመጡበት ለመመለስ እንደሚገደዱ አስታውቀዋል።በኢትዮጵያ 9 መቶሺህ የሚደርሱ የኤርትራ የሱማሊያና የድቡብ ሱዳን ስደተኞች ይኖራሉ።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-10
