
አብዛኛው አካባቢ በሰላም በተጠናቀቀው የኬንያ ምርጫ ዜጎች ውጤት እየጠበቁ ነው። ለመራጭነት ከተመዘገበው 22 ሚሊየን ዜጋ 55 በመቶው ድምፅ በሰጠበት በዚህ ምርጫ ከአራቱ እጩዎች ሁለቱ የበለጠ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተጠብቋል።
ከምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶና ከረጅም ጊዜ ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ማንኛው አብላጫውን ድምፅ አግኝቶ ስልጣኑን ይረከባል የሚለው ኬንያውያን በጉጉት የሚጠብቁት ነው።
ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ይህ ምርጫ ከጥቃቅን ችግሮች ውጪ በሰላም መጠናቀቁ ግን ለኬኒያውያን እፎይታ መስጠቱን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-10