አሜሪካ ግዙፍ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ማምረቻ ማዐከልና የምርምር ተቋም ልትገነባ ነው። ይህ የቴክኖሎጂ ማእከል እውን እንዲሆን የተመደበውን የ2መቶ 50 ቢሊዮን ዶላር በጀት ፕሬዝዳንት ጆባይደን አጸድቀዋል።
የቴክኖሎጂ ልማቱ አሜሪካ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በቻይና እየተበለጠች ነው የሚለውን ሥጋት የሚቀርፍ ነው ተብሎለታል።በሀገሪቱ የኮምፒውተር ቺፕስ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ለሚገነቡ ኩባንያዎች የታክስ እፎይታን ይሰጣልም ተብሏል።
ለሚቀጥሉት አንድመቶ ዓመታት የአሜሪካን መሪነት እና ብልጽግና የሚያረጋግጥ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክት ነው ሱሉ አንድ ክፍተኛ የሴኔት አባል ተናግረዋል። የአውሮፓ ኀብረትም በተመሳሳይ የኮምፒውተር ቺፕስ ምርቶችን ለማሳደግ በዚህ አመት 40 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚመድብ ማስታውቁ ይታወሳል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-10
