ሀገሬ ቲቪ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማብራሪያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመንግስትና በህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር በአፋሪካ ህብረት ብቻ መመራት አለበት አለ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬዉ ዕለት በሰጡት መግለጫ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርድሩን በገንዘብና በቴክኒክ መደገፍ እንደሚችል ገልጸው፤ ከዚያ ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ብለዋል።

ድርድሩን የሚመሩት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦሊሰጉን ኦባሳንጆ የአደራዳሪ ኮሚቴዎችን ከአፍሪካ ሀገራት ማካተት እንደሚችሉም በመግለጫው ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑ በሱዳንና በግብጽ አካባቢዎች የተከሰተው ጎርፍ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ቢከናወንም በአገራቱ የውሃ አቅርቦት ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ያሳየ ነው ሲሉ አምባሳደር ተናግረዋል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-11