የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከጎርጎሮሳውያኑ ሚያዝያ ወር ጀምሮ 4,765 የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች ወደ ትግራይ ገብተዋል አለ።
ኮሚሽኑ ከመቀሌ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የሚያደረገው የእርዳታ አቅርቦት በነዳጅ እጥረት እየተስተጓጎለ ነው ብሏል።
ዩኤንኤችሲአር በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ያልተረጋጋ በመሆኑ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ተቋማትን እየገደበ መሆኑን መግለጹን ዥንዋ ጽፏል።
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን በማነጋገርና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆንኩ እወቁልኝ ብሏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-11
