ሀገሬ ቲቪ

ሴራሊዮን የሰዐት እላፊ ጣለች

በሴራሊዮን በተከሰተው የዋጋ ግሽበት፣ የነዳጅ መወደድ ምክንያት የኑሮ ውድነት ከአቅማችን በላይ ሆኗል ያሉ ነዋሪዎች ሕዝባዊ አመጽ ቀስቅሰዋል። በዚህ አመጽ እስካሁን ሁለት ንጹሀን እና አንድ የጸጥታ ኃይል አባል መሞታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

የሴሪላሊዮን መንግሥት አመጹን ለማብረድ የሰዐት እላፊ መጣሉም ተሰምቷል። በመላ ሀገሪቱ ከምሽት 3 ሰዐት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

“እንደ መንግሥት እያንዳንዱን ዜጋ የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፤ የተከሰተው ነገር አሳዝኖናል” ሲሉ የሀገሪቱ ፐሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ቢዮ በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል። በተጨማሪ መንግሥት ክስተቱን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያጣራ ፐሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-11