ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካን ኢኮኖሚ መዳከሙን ቀጥሏል

በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረትና የዋጋ ንርት እየተፈተኑ ነው ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያና ናይጄሪያን ጨምሮ፣ 80 ሀገሮች ውስጥ ለሚገኙ 138 ሚሊዮን ሰዎች ለሚያደርግው የምግብ እህል ድጋፍ አቅርቦቱን የሚያገኘው ከአውሮፓ ሀገራት መሆኑ አሳውቋል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከ346 ሚሊዮን የሚልቁ አፍሪካውያን የምግብ እጥረት የሚገጥማቸው ሲሆን ለጉዳዩ መፍትሔ ካልተበጀለት በየቀኑ መመገብ የማይችሉ ስዎች ቁጥራቸው ቀላል አይሆንም ብሏል፡፡

ዩኒሴፍም ባወጣው ተመሳሳይ ሪፖርት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ በአፍሪካ 11 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ከፋ ረሃብ ያመራሉ ሲልስጋቱን አስቀምጧል።

ያልተቋረጠው ድርቅ፣ የዝናብ እጥረትና በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ያሉት ግጭቶች፣ የአፍሪካን የምግብ ችግር እንዳያባብሰው ከወደሁ ተፈርቷል።

ቦአዝ ኬይዚር ጥምረት ለአረንጓዴ አብዮት የፖሊሲ ኃላፊ ናቸው። ሃላፊው ከአፍሪካን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የኑሮ ውድነቱን የአህጉሪቱ ህዝቡ መሽከም ከሚችለው በላይ እየሆነበት ነው።

ሃላፊው የሽቀጦች ዋጋ አልቀመስ ማለት ፖለቲካው እንዳይረጋጋ ያደርገዋል ሲሉም ለአፍሪካን ኒውስ አውርተዋል ፤ የአፍሪካ መንግስታት እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዋጋ ለመቀነስ እየሰሩት ያለውን ስራ እንዴት ያዩታል ተብለው የተጠየቁት ሃላፊው ይህንን ብለዋል።

መንግስታት አካባቢን ሳያስተጓጉሉ ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባቸው በሃላፊው ተናግረዋል።

የሩሲያ ዩክሬን ቀውስ ለአፍሪካ የመጀመሪያው ቀውስ አይደለም አህጉሪቱ በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ እና በአንበጣ መንጋ ዋጋ ስትከፍል ቆይታለች ብለዋል።

በሩዋንዳ ኪጋሊ የሚካሄደው የዘንድሮው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ፎረም መንግስታት እና የንግድ መሪዎች በመፍትሄዎች ላይ እንዲወያዩ እና እንዲስማሙ እድል የሚሰጥ በመሆኑም ተስፋ ተጥሎበታል።

የአፍሪካ ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም፤ ትልቁ ፈተና ቅንጅት ማጣት ነው የሚሉት ሃላፊው የአፍሪካን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ ማፋጠን የሚያስችሉ የውሳኔ ሃሳቦችን ማሳለፍ ከጉባኤው እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።

በአፍሪካ አገራት የእርስ በእርስ ንግድ 16 በመቶ ብቻ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-12