ሀገሬ ቲቪ

አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊያለሙ መሆኑ ተሰማ ።ፓርኩን ለመገንባት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከቻይናው ዎዳ ብረታ ብረት ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።

ፓርኩ በ95 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በሰበታ ከተማ ይገነባል ሲል ዥንዋ ጽፏል። ከ400 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ኢንቨስትመንት ይስባል ተብሎም ይጠበቃል።

ፓርኩ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት እቃዎች፣ ጎማ እና ኤሌክትሪክ ባትሪዎችን በማምረት ለኢትዮጵያ እና ምስራቅ አፍሪካ ገበያ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-12