ሀገሬ ቲቪ

የሕዳሴ ግድብ ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቀቀ

ሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራውን ያሳረፍበትና ስኬቱን በጉጉት የሚጠብቀው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ቁመቱን ከአምናው በ25 ሜትር ጨምሮ ከባህር ጠለል ከ6 መቶ ሜትር በላይ ሞልቶ መፍሰሱን ጀምሯል።

በትላንትናው ዕለት 375 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችለውን ሁለተኛውን ተርባይን ያንቀሳቀሰው የህዳሴው ግድብ ዛሬ ደግሞ ሶስተኛው ዙር የውኃ ሙሌትን አሳክቷል። ይህ ስኬት ለአፍሪካውያን ጭምር ነው ብልዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ለውጤታማነቱ ቀን ከሌት የለፉና በያሉበት የበኩላቸውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያንም በፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተመስግነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት አባይ በተለይ ለሶስቱ ሀገራት ለኢትዮጵያ ለሱዳን ለግብጽ የተሰጠ የፈጣሪ ሰጦታ በመሆኑ በጋራ በመጠቀም ልንለማበት እንጂ የጠብ ምክንያት ሊሆን አይግባምየህዳሴው ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት 83 ነጥብ 3 በመቶ የደረሰ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-08-12