ሀገሬ ቲቪ

ከተማ አስተዳደሩ ያስገነባውን መንገድ አስመረቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባውን የሳርቤት - ጎፋ ማዞርያ - የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ዛሬ አስመርቋል።

ይህ መንገድ ከአሌክሳደር ፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ድረስ 3.8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ30 እስከ 45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት አለው ተብሏል።

በተጨማሪም በአንድ ጊዜ በርካታ ተሸከርካሪዎችን ሊያሳልፍ በሚያስችል ስፋት ከመገንባቱም በላይ 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ በውስጡ ይዟል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-15