በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከይዞታ ጋር በተያያዘ ተጥሎ የነበረው ዕግድ ተነሳ፡፡ ዕግዱ ከታኅሳስ 12 ቀን 2014 ጀምሮ መነሳቱን የከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ በሆኑት አቶ ጥላሁን ወርቁ ሮቢ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ያመላክታል፡፡ ዕግድ ተጥሎባቸው ከነበሩት ውስጥ በሊዝ ይዞታዎች አዲስ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣ የፕላን ስምምነት፣ የግንባታ ማሻሻያ፣ ለነባር ይዞታ ካርታ ያላቸው በመልሶ ማልማት ውስጥ የተጠናላቸው የሊዝ ይዞታዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የምትክ ቦታ መሬት ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የዕድሳት ፈቃድ መስጠት፣ የግንባታ ማስጀመሪያ የመስጠትና አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የግንባታ ማስጀመሪያ ክትትል ውስጥ የነበሩ በዕርከን የአገልግሎት ገቢ የመሰብሰብ ጋር ተያይዞ ተጥሎ የነበረው እግድ ነው የተነሳው፡፡ እንዲሁም ለተለያዩ አካላት የግንባታ መረጃ የመስክ ሪፖርት የመስጠትና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ መስጠትና ክፍያ የመሰብሰብ የአገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-23
