የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደምታጠናክር ገለጹ ።
ፕሬዝዳንቱ ሰሜን ኮሪያ ከጃፓን አገዛዝ ነጻ የወጣችበትን ቀን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ ደብዳቤ ጽፈዋል። በደብዳቤያቸው ሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻቸውን እንደሚያጠናክሩ የገለጹ ሲሆን ይህም በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ሰላምና መረጋጋት ይበልጥ ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል ብለዋል።
ሰሜን ኮሪያ ከጃፓን አገዛዝ ነጻ የወጣችበትን ቀን ዛሬ ለ77ኛ ጊዜ በወታደራዊና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እያከበረች ትገኛለች ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-15
