ዛሬ ዛሬ እንስሳትን በሰዎች ስራ ውስጥ እንደ አጋዥ መመልከት አዲስ አይደለም።
ውሾችን በምርመራ ስራ ውስጥ በማሽተት ችሎታቸው መጠቀም፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ፈንጂዎችን ለማምከን የሰለጠኑ አይጦችን መጠቀም አዲስ አይደለም።
ከወደ ሳን ፍራንሲስኮ የባቡር ጣቢያ ውስጥ የበዙት እርግቦች ለባቡር ጣቢያው ኃላፊዎች ሃሳብ ውስጥ ይከታቸዋል።
ከምንም በላይ ደግሞ እዚህ እኛው ሀገር ሲሳይ ነው ስንል የምናልፈውን፤ እነዚህ እርግቦች በተሳፋሪዎች ላይ ኩሳቸውን እየጣሉ ማስቸገራቸው ነበር።
ኃላፊዎቹ በምሬት ብቻም አልቆሙም የእርግቦቹን ጠላት የሆነውን ጭልፊት በባቡር ጣቢያው ለጥበቃ ቀጠሩ።
በኤል ሴሪቶ ዴል ኖርቴ የባቡር ጣቢያ ስራውን የጀመረው የ5 ዓመቱ ጭልፊት አሁን ተቆጣጣሪው ሪኪ ኦርቲዝ ጋር በጣቢያው ሲንጎማለል ይውላል።
ለወትሮ ተሳፋሪዎች ከባቡር ሲወርዱ እና ለመሳፈር ወደ ጣቢያው ሲመጡ ፈተና የሚሆንባቸው የእነዚህ እርግቦች ነገር አሁን መላውን አግኝቷል። አዳኙ ጭልፊት እና አለቃው በሳምንት ሦስት ግዜ ጣቢያውን በመዞር ቅኝት ያደርጋሉ።
ሪኪ ኦርቲዝ ስለሁኔታው እንዲህ ይላል።
“በዚህ በባቡር ጣቢያ ውስጥ ከጀርባዬ በምትመለከቱት የጣራ ርብራብ ላይ ከ15 እስከ 20 የሚደርሱ እርግቦች ነበሩ። ከመጀመሪያው ሳምንት ቦታውን የማካለል ስራ በኋላ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እርግቦች እዚህ የሉም።”
እኚህ በራሪ ፍጥረታት ከልብ በደንብ ይተዋወቃሉ ኦርቲዝ እንደሚለው፣ እርግቦቹ ከተፈጥሯዊ አዳኛቸው እራሳቸውን ለመጠበቅ ከእርሱ መራቅን ይመርጣሉ።
አስቀድሞም ቢሆን ለአንድ ሳምንት ያህል ይህ አዳኝ በባቡር ጣቢያው ውስጥ የራሱን የሆነ ግዛት መስርቷል።
መቼም ረሀብ ክፉ ነው ታዲያ ይሄው አዳኝ ጭልፊት በመራቡ ሳቢያ ከባቡር ጣቢያ በጥቂት ርቀት ላይ አዲስ ማረፊያ ያበጁትን እርግቦች አደን እንዳየንዳይገባ አልያም በስፍራው የሚመጡ ተሳፋሪዎችን ወደ መተንኮስ እንዳይሻገር ኦርቲዝ ያለመርሳት ቀለቡን ያቀብለዋል።
“የቀን ውሏችንን የምንጀምረው ከመግቢያው ከስረናው ወለል ላይ ነው በባቡር ጣቢያው የውስተኛው ክፍል በጣሪያው መዋቅር ላይ እና መኖር አለመኖራቸውን እነመለከታለን ካሉም አባረን እናስወጣቸዋለን።”
በጭልፊቱ ስራ የባቡር ተርሚናሉን የሚጠቀሙ ተሳፋሪዎችም ደስተኛ ናቸው።
“በዚህ አይነት ዘዴ መምጣት የሚጠበቅ አይደለም። በጣል ደስ የሚል እንስሳ ነው።”
“በዚህ ቦታ ላይ ያለውን የእርግቦች ችግር ለመፍታት የተሻለው መንገድ ነው። በርካታ ሰዎች ይመግቧቸው ነበር ማድረግ ባይጠበቅባቸውም ያው በጉልበት አይሆንም። ነገር ግን ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ይህ ጥሩ መንገድ ነው።”
የባቡር ጣቢያው ለእነዚህ እርግቦች ጭልፊትን ከመቅጠር ባለፈም በሚያርፉበቸው ቦታዎች ላይ እሾህ መሰል ነገር በማስቀመጥ በቦታው ላይ እርግቦች እንዳይያርፉ ለምድረግ እየሞከረ ይገኛል።
ለነገሩ ለጆሯችን እርቆ እንጂ ጭልፊቶችን እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች የመጠቀሙ ነገር አልፎ አልፎ ይስተዋል እንደነበር ሰምተናል። በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሞል በእርግቦች የተነሳ ደንበኞቼ ተማረሩ ሰል ተመሳሳይ እርምጃን ወስዶ ነበር።
ተፈጥሮ ለአንዱ ችግራችን ሌላ መፍትሄ በራሷ ውስጥ ታቅፋለች።
በሳምሶን ገድሉ
2022-08-15
