60ኛ ዓመት የምሥረታ በዐሉን በቅርቡ ያከበረው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ‘አድማስ ሎተሪ’ የተባለ የዲጂታል ሎተሪ ከወራት በፊት አስጀምሯል። ዛሬ ነሐሴ 09/2014ዓ.ም ታዲያ የዚሁ የዲጂታል ሎተሪ እጣ የመቁረጡ ጊዜ ከለሊቱ ስድሰዓት ይጠናቀቃል።
ሞባይልን በመጠቀም ሎተሪ የቆረጡ ሰዎች ቁጥር በሙከራ ደረጃ መደበኛውን ሎተሪ ከሚቆርጡ ዜጎች ጋር ተቀራራቢ እንደኾነ በተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቴውድሮስ ንዋይ ነግረውናል።
ዲጂታል ሎተሪውን የቆረጡ ደንበኞችን ቁጥር እና የተገኘውን ገንዘብ አሁን ላይ ይፋ ማድረግ እንደማይቻል ነው የገለጹልን።
ብሔራዊ ሎተሪ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ከወረቀት ሎተሪው የተለዩ ጨዋታዎችን ለመጀመር እቅድ ይዞ ወደ ሥራ ገብቷል። ‘’አድማስ ሎተሪ’’ የተባለው የዲጂታል ሎተሪም የዚህ ዕቅድ አንድ እርምጃ እንደኾነ አቶ ቴውድሮስ ተናግረዋል።
ከዲጂታል ዓለሙ ከደህንነት አንጻር የሚያግጥሙ የተለይዩ ችግሮች መኖራቸው ይነሳል ከዚህ ረገድ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ የደህንነት ችግር እንደማያሰጋው ተናግሯል።
የዲጂታል ሎተሪው እያደገ መሔድ በወረቀት የሚታተሙ ሎተሪዎችን በመሸጥ በሚተዳደሩ ዜጎች ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ እንደማይኖር ሰምተናል‘አድማስ ሎተሪ የተሰኘው የዲጂታል ሎተሪ ለባለዕድለኞች እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ነው።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-15
