ሀገሬ ቲቪ

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ ሀገር ቤት በግዢ እየገባ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3 አመታት ያክል አግዶት የቆየውን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ ሀገር ቤት እያስገባ መሆኑ ተሰማ ። በመጋቢት 2011 ዓ.ም. ቦይንግ ማክስ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፉ ይታወሳል።

አየር መንገዱ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑን ማሻሻያ እና ዲዛይን በጥልቀት መርምሬያለሁ ብሏል። ሶስት አውሮፕላኖች ለአየር መንገዱ የደረሱ ሲሆን ሌሎችም ተጨማሪ አውሮፕላኖችን አየር መንገዱ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኑን ወደነበረበት የበረራ አገልግሎት እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ ስራ አሰማርቷል ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-16