ሀገሬ ቲቪ

10 ሚሊዮን የዲጂታል መታወቂያ የመስጠት ዕቅድ እንዳለ ተጠቆመ

ሀገራችን በ2015 በጀት አመት 10 ሚሊዮን የዲጂታል መታወቂያ የመስጠት ዕቅድ አላት ተባለ። ይሄንንው ማስፈጸም የሚያስችል ህግም መጽደቁ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ላይ ላለው የዲጂታል መታወቂያ 100 ሺህ ሰዎችን ለሙከራ አገልግሎቱ መመዝገቡን አስታውቋል።

ፕሮግራሙ ለአገልግሎቱ የሃርድዌር እና ሶፍትዌር መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር እየሰራ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

በአብርሃም በለጠ
2022-08-16