ሀገሬ ቲቪ

ማሊ የፈረንሳይ ወታደሮች መውጣት በሰላሜ ላይ ለውጥ አያመጣም አለች

የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ የፈረንሳይ ወታደሮች ከሀገሪቱ መውጣታቸው በሰላሟ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም ማለቷ ተሰማ።

የፈረንሳይ ወታደሮች ለአስርት ዓመታት እስላማዊ ታጣቂዎችን ለመዋጋት በሚል በሀገሪቱ ቆይተዋል። ማሊ ፈረንሳይ ወታደሮቿን ከሀገሪቱ እንድታስወጣ ባስተላለፈችው ትዕዛዝ ወታደሮቹ ከሀገሪቱ ወጥተዋል።

የሀገሪቱ የቀድሞ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይ የማሊ ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ ትሻለች። የፈረንሳይ ወታደሮች መኖር ሀገሪቱን ከታጣቂዎች ጥቃት አላዳናትም በሚል ማሊያውያን የፈረንሳይ ወታደሮች እንዲወጡ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ነበር። መረጃው የአፍሪካ ኒውስ ነው።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-16