የሊቢያ ምርጫ መራዘሙን ተከትሎ አሜሪካ ቁጣዋን ገለጸች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ እና በሊቢያ አምባሳደር ሪቻርድ ኖርላንድ ናቸው የሊቢያን ምርጫ መራዘም የኮነኑት፡፡ ሊቢያ ከዛሬ ጀምሮ አስከሚቀጥለው ወር ምርጫ የማደርግበት ጊዜ ነው ስትል ቀን ቆርጣ ነበር፡፡ ሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ሊያደረግ የነበረው ፕሬዝዳንዊ ምርጫ በተባለው ዕለት ማድረግ እንደማይቻል ማሳወቁን ተከትሎ ነው አምባሳደር ኖርላንድ አሜሪካን ወክለው ወቀሳ ያቀረቡት፡፡ የምርጫውን ሂደት ለመከታተል የተቋቋመው የፓርላማ ኮሚቴ የመጀመሪያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ የማይቻል ነው ማለቱን ተከትሎ ነው ምርጫው ለሚቀጥለው ወር እንዲዛወር የተወሰነው፡፡ የሊቢያ ሹማምንት ከሊቢያ ሕዝብ ጎን በመሆን ከምርጫው ጋር ተያይዞ ያሉትን የህግ እና የፖለቲካ መሰናክሎች ማሳወቅ እንዳለባቸው እና ተወዳዳሪ እጩዎችን ዝርዝር ማጠናቀቅን የመሳሰሉ ተግባራትን በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አሜሪካ አሳስባለች፡ ከጠንካራ ህዝባዊ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ለምርጫ መስራት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አምባሳደር ኖርላንድ ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም የሊቢያን የወደፊት ዕጣፈንታ ይወስናል የተባለው ምርጫ መራዘሙ ሊቢያውያን የተሰማቸውን ቅሬታ እና ቁጣ አሜሪካ ትጋራለች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-23
