ሀገሬ ቲቪ

ቻይና የታይዋን ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች

ቻይና ነጻ የታይዋን ሀገርን ለመመስረት እየተንቀሳቀሱ ነው ባለቻቸው ሰባት የግዛቲቱ ባለስልጣናት ላይ ማእቀብ ጣለች።

ማእቀቡ ባለስልጣናቱ ወደ ቻይናና ሆንግ ኮንግ እንዳያመሩ በእነርሱ የሚመራ ማንኛውም ተቋምና ድርጅት ከቻይና ጋር የኢኮኖሚ ትብብር እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው።

ቻይና ማእቀቡ የሀገር አንድንትን ለማስጠብቅና ታይዋንን ለመነጠል የሚደረግ የምዕራብያውያንን ሴራ ለማክሽፍ ያለመነው ብላለች።

ባለስልጣናቱ ከድርጊታችው ካልታቀቡና ታይዋን የቻይና ሉዓላዊ ግዛት አካል እንደሆነች የሚያረጋግጠውን የአንድ ቻይና ፖሊስን ተቀብለው የማይሄዱ ከሆን የዕድሜልክ ዕገዳ ሊጣልባቸው እንደሚችልም ተገልጿል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-16