ሀገሬ ቲቪ

ኳስ ሜዳም የባቡር መንገድም የሆነው ስታዲየም

በዘመናዊ መልኩ በ19ው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎች ላይ በእንግሊዝ ስለመጀመሩ መዛግብት ይናገራሉ።

ስርዓት ተሰርቶለት በዘመናዊ መልኩ መደረግ የጀመረው እግር ኳስ በሰፋ መስክ ላይ ያለከልካይ ከመሮጥ እስከ ተከለለ እና ተቆጠበ ሜዳ፤ ለቁጥር ከሚበዙ ተጫዋቾች እስከ 11 ሆኖ መጫዎት፣ በፈረስ ላይ ተቀምጦ ከመዳኘት በቪዲዮ እስከ ታገዘ የዳኝነት ስርዓት ሁሉም በእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ያለፉ ናቸው።

ከዚህ ሁሉ መሀል ኳስን ለመጫዎት የተከለለ ሜዳ እና የተጠበቀ ሜዳ ዋነኛው ነው። ታዲያ በዚህ ዘመን በእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ የሚያልፍ የባቡር መስመር ስለመኖሩ ብንነግሮትስ።

ይህ ኳስ አብዝቶ በሚወደድባት አውሮፓ ውስጥ ብቻ የሚያዩት ሀቅ ነው። የስሎቫኪያ አማተር የእግር ኳስ ክለብ ቲጄ ታትራን ሲየር ባሎግ እስታዲየም ከወትሮ የተለየ ነው።

በዚህ ዘመን በሙዚየም ውስጥ ናቸው ብለው የሚያስቧቸው በድንጋይ ከሰል እና በእንፋሎት የሚሰሩ ባቡሮች የሜዳውን ጥግ ታከው ከተመልካቾች ፊት እና በሜዳው ጠርዝ ጋር ታኮ ያልፋል።

ከ5 ሺሕ ብዙም ያልዘለለ ነዋሪ ያለባት የስሎቫኪያዋ ከተማ ሲየርኒ ባሎግ ከሰባት ዓመታት ወዲህ የጎብኚዎች መዳረሻ ወደመሆን ተሻግራለች።

ምስጋና ለዚህ እግር ኳስ ሜዳ ይሁን እና በ2007 ዓ.ም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴላይ ብቅ ያለው የዚህ ሜዳ ነገር በርካቶችን ቀልባቸውን ገዝቷል።

ነገሩ ለአንድ ግዜ ብቻ የሆነ ሊመስሎ ይችላል፤ እውነታው ግን በዚህ እስታዲየም ውስጥ በእንፋሎት የሚሰራ የቱሪስት ማመላለሻ ባቡር በዚያ ያልፋ።

ይህ የስሎቫኪያ ከተማ ስታዲየም በ1970ዎቹ ስለመገንባቱ ይነገራል። የከተማ አስተዳደሩ ለምን ይህንን ቦታ ለስታዲየም መገንቢያነት እንደመረጠ ግን የተቀመጠ ምንም ምክንያት የለም።

በ1980ዎቹ የሀገሬው ጎምቱ ሰዎች የባቡር መስመሮችን ማሳደስ ሲጀምሩ ነገሮች በተቃራኒው ሆነ። ስታዲየሙ ስታዲየም ብቻ ሳይሆን የባቡር መስመር መተላለፊያም ጭምር የመሆን እጣ ገጠመው።

በ1982 ዓ.ም ቱሪስቶች በዚህ እስታዲየም ውስጥ በእንፋሎት ባቡር ተሳፍረው የሚደረገውን ጨዋታ በቁንፅል ተመልክተው ያልፉ ጀመረ።

ታዲያ 17 ኪሎሜትር በሚረዝመው በዚህ የባቡር መስመር ቱሪስቶች ከሚመለከቷቸው ነገሮች መካከል ስታዲየሙ አንደኛው ነው። በበጋ ወራት በዚህ ባቡር ለመሳፈር ትኬትን የሚፈልጉ ጎብኚዎች ቁጥር ይበረክታል።

የተጫዋቾቹ ነገር ደግሞ ሌላ ነው፤ ባቡሩ እያጓራ በሜዳው በሚያልፍበት ወቅት ከሜጤፍም ሳይቆትሩት ጨዋታቸውን ያደሩታል።

ታዲያ ጨዋታውን ለመመልከት በሜዳው የተገኙ ገሚሱ ጎብኚዎችን በአጀብ ሰላም ሲል ገሚሱ ደግሞ ጨዋታውን በትኩረት ለመከታተል ይሞክራል።

ይህ ሁሉ መዝናናትንም፣ ጉብኝትንም፣ ኳስ ጨዋታንም አብሮ በያዘው ስታዲየም የሚሆን ነው።

በሳምሶን ገድሉ
2022-08-16