ሀገሬ ቲቪ

ከፍተኛ ዝናብ የተመዘገበበት ክረምት

ወቅቶች መፈራረቃቸው የተፈጥሮ ህግ ነው። ግንቦትን ተሻግሮ ሰኔ ሲመጣ የክረምቱ መግባት ይበሰራል። ታዲያ ከክረምቶች ሁሉ የዘንድሮው ክረምት ከወትሮ የተለየ ስለመሆኑ በርካቶች ያነሳሉ።

ለፍቶ ማደር ሰርቶ መለወጥን ሽተው ኑሯቸውን ከጎዳናው ጥግ ላይ ያደረጉ ታታሪዎች እያገባደድነው ባለው ክረምት የበለጠ ተቸግረናል ይላሉ።

ይህንን ሀሳብ ባለሙያውም ይስማሙበታል። አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ሜቲሪዮሎጂ ኢንስቲቲውት አማካሪ እና ተመራማሪ ናቸው የዘንድሮው ክረምት ከወትሮ የተለየ የዝናብ ስርጭት ሊኖር እንደሚችል አስቀድሞ ስለመተንበዩ ነግረውናል።

ታዲያ ይሄው የዝናብ ስርጭት እንደ ባህር ዳር ባሉ አካባቢዎች ከ30 ዓመታት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅበት ሁኔታ በዝናብ መለኪያ በ24 ሰዓት ውስጥ እስከ 110 ሚሊ ሜትር የደረሰ ዝናብን አግኝተው ነበር። በነቀምቴም በተመሳሳይ እስከ 135 የሚደርስ የዝናብ መጠንን በ24 ሰዓት ውስጥ ማግኘት ችለዋል።

በመዲናችን አዲስ አበባም እስከ 71 ሚሊ ሜትር የደረሰ ከበድ ያለ ዝናብ ታይቶ እንደነበር ባለሙያው አጫውተውናል።

ይሄው የወቅቶች መፈራረቅ የዘንድሮውን ክረምት እንዲከብድ ያደረገው በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የተፈጠረው የመቀዝቀዝ ሁኔታ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-08-17