ሀገሬ ቲቪ

የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት ተጠናክሯል

ሩሲያን ጨምሮ ኃያላኑ አገሮች ከአፍሪካ ጋር የተሻለ ጥምረት ለመፍጠር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ሁሉም አገሮች የየራሳቸውን አገራዊ ጥቅም ለማስከበር የሚሯሯጡ ቢሆንም ።

ካለፉት አስርት ዓመታት በፊት የአፍሪካና የሩሲያ ግንኙነት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ሩሲያ ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት ለመስጠት እየሞከረች ነው ከዩክሬን ጋር በገባችው ጦርነት ከበርካታ ምዕራብያውያን ሀገሮች ጋር ይበልጡኑ የተኳረፍችው ሩሲያ የአህጉሪቱን ድጋፍ ለማግኘት ደፋ ቀና እያለች ነው ።

ምዕራባውያን ሩሲያ በአፍሪካ ተጽዕኖዋን ለማስፋት መጣሯን በአይነ ቁራኛ እየተከታተሉት ነው ጥቅማችንን ያሳጣን ይሆን ወይ በሚል።

አፍሪካ በሩሲያ የውጭ ፖሊሲ ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት ቅድሚያ የማይስጣጥ ሆና ሳለች አሁን ከፖሊሲዋ በተጻራሪ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የምታደርገውን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብር ማጠናከሯ ወዳጅ ስታጣ እንዳይሆን የሚሉም አሉ።

ምዕራባውያን ሀገራት ከጣሉባት ማዕቀብ ለማምለጥ በሚል አዲስ የንግድ እና የጂኦፖለቲካዊ እድሎች ላይ በማማተሯ ነው አፍሪካን የተወዳጀችው እየተባለ ነው።

ገፊ ምክንያቷ ምንም ይሁን ምን አሁን ላይ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ መጠን አሳድጋለች። የሚዲያ ሽፋኗንም እንዲሁ ።

ለሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ጨዋታ ቀያሪ ነው የሚባለውን የሩሲያ-አፍሪካ የመጀመሪያ ስብሰባ በ2019 እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በሶቺ አካሂዳለች።

በሀገራቱ መካከል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትብብርን መፍጠር ባለመው በዚህ ጉባኤ ከ54ቱም የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮችም ተሳትፈዋል። ከዚህም ውስጥ 45 በርዕሰ ብሔሮቻቸው መወካላቸው አፍሪካውያኑም ወዳጅነቱን እንድሚሹ ያሳየ ነው ተብሎለታል።

በጉባዔው ላይም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "በአፍሪካ ሀገራት መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን ማጠናከር አሁን የሩሲያ የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው" ብለው ነበር ።

በጉባዔው ላይ እንደተገለጸው በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ በ2024 ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል በሚል ተተንብዮ ነበር ።

በ2020 የንግድ መጠኑ ወደ 14 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ዝቅ ማለቱን እና በዩክሬን ያለውን ጦርነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ግን ይህ ግብ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ይፈጸማል ወይ የሚለው አጠያያቂ ቢሆንም ።

ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በጎጎሮሳውያኑ 2022 በአዲስ አበባ ለማካሄድ ውጥን ቢያዝም ይሄ ነው ባልተባለ ምክንያት እስከ 2023 አጋማሽ ድረስ እንዲራዘም ሆኗል።

የጉባኤው መራዘም ግንኙነቱን ዳግም እንዳያሳሳው የሰጉት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሀምሌ ወር በተመረጡ የአፍሪካ ጉብኝት አድርገዋል።

ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ የጉብኝጥ መዳረሻዎች ነበሩ። ይህ ጉብኝት በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አፈሪካውያን ገለልተኛ ሆነው በመቆማቸው ለማመስገን ያለመም ነው።

በሌላ በኩል, ከምዕራብያውያኑ መገለል እየደረሰባት በመሆኗ የላቭሮቭ የአፍሪካ ጉዞ ሩሲያ አሁንም አጋሮች እንዳሏት ለማሳየት ነበር የሚሉ አሉ።

የላቭሮቭ ጉብኝት ከዩክሬን ጋር በገባችው ጦርነት ሳቢያ በአፍሪካ ለተከሰተው የምግብ ቀውስ ተጠያቂ እንዳልሆነች ለማረጋገጥ የተኬደ ርቀት እንደሆነም ተነግሯል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን በዩክሬን በተካሄደው ጦርነት “የምግብ ዋስትና እጦት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል” ይላል። ሩሲያ እና ዩክሬን በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የግብርና ምርቶች አምራቾች እና ላኪዎች በመሆናቸው።

ወደ ወታደራዊ ትብብር ስንመጣ ሩሲያ የአፍሪካ ትልቁ የጦር መሳሪያ አቅራቢ ነች። ወደ አፍሪካ ከሚገባው የጦር መሳሪያ ግማሽ ያህሉ ከሩሲያ ነው ።

የሩስያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ እነዚህን ወታደራዊ ግንኙነቶች የበለጠ አስፋፍቷል። በተጨማሪም፣ ሮሳቶም፣ የሩሲያ ግዛት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ እና ከሩዋንዳ ጋር ሁለት አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።

በጠቅላላው እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ስምምነቶች በመጀመሪያው ሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተደርሷል።

ስምምነቶቹ በህግ አይን ሲታዩ አስገዳጅ ባህሪ ስለሌላቸው አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛ ኢንቨስትመንት ላያመሩ ይችላሉ የሚል ስጋት የገባቸው ወገኖች ግንአ ልጠፉም።

የቀጣዩ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎች ንግድ፣ የተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ኢነርጂ እና ደህንነትን እና ሌሎች ጉዳዮችላይ እንደሚያተኩር ከወዲሁ ታውቋል።

ይህ ትብብር ወደፊት ወደ ጠንካራ የፖሊሲ አጋርነት ያመራል ወይ የሚለው ወደ ፊት የሚታይ ይሆናል። ምንም ይሁን ምን የሩሲያ ለአፍሪካ ትኩረት መስጠት የምዕራቡ ዓለም ሳይወድ ትኩረቱን በአፍሪካ እንዲያደርግ አስገድዶታል ።

ለዚህ ማሳያው ላቭሮቭ እግራቸው እንደወጣ የአሜሪካ አቻችው አንቶኒዮ ብሊንከን አፍርካን መዳረሻቸው ማድረጋቸው ነው።

ይህ ሁሉ ርብርብ ከፉክክር ባልፈ አህጉሪቱን እንዲጥቅም አድርጎ መቃኘት ግን ከተፎካካሪዎቹ ይልቅ የአፍሪካ መሪዎችን ሊያስቡበት ይገባል የፎሪን ፖሊስ እይታ ነው።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-17