ሀገሬ ቲቪ

የአደረጃጀት ክለሳ የተደረገባቸው ሚሲዮኖች ለውጥ አስገኙ

መንግሥት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኤምባሲዎች፣ ሚሲዮኖች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል ስምሪትና በአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ ማሻሻያ መደረጉ ለውጥ አምጥቶልኛል አለ።

ይህ የተባለው የአደረጃጀት ለውጥ በተደረገባቸው ሚሲዮኖች ላይ የግምገማ ውይይት በተካሔደበት ወቅት ነው።የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት፣ በትግበራው ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች ካሉም በየጊዜው እየፈተሹ ማስተካከያ ማድረግ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናግረዋል።

የማሻሻያ እና የአደረጃጀት ክለሳ የተደረገባቸው ሚሲዮኖች እንደአስፈላጊነቱ ተለይተው የሰው ሀይል ስምሪት እና የበጀት ድልድል እንዲኖራቸው ይደረጋልም ተብሏል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-17